ከበሮ ፨ Kebero
ከበሮ ፨ Kebero
ከበሮ ፨ Kebero

ከበሮ ፨ Kebero

Regular price $150 Unit price  per 

Shipping calculated at checkout.
#ከበሮ ማለት ከበረው ከሚል የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ደፋ፣ መታ፣ ከረከረ፣ ቆረቆረ፣ ጎሰመ፣ ማለት ነው፡፡
ከበሮ የጌታችን ተምሳሌት ነው፡፡
.የከበሮ ጠፈሩ -ጌታ በአይሁድ እጅ ሲገረፍ የወጣበት ሰንበር ተምስሌት ነው፡፡
.አንድም -ጌታችን የተገነዘበት ገመድ ምስሌ ነው፡፡
.አንድም - የታሰረበትና የተጎተተበት የተሰቀለበት ገመድ ምስሌ ነው፡፡
#የከበሮ_ጨርቅ - ቀይ ጨርቅ መሆን ይኖርበታል
.ቀይ መሆኑ - ጌታ ሲሰቀል ለብሶት የነበረ ቀይ ልብስ ከለሜዳ ተምሳሌት ነው፡፡
.አንድም የከበሮ ጨርቅ -ጌታ የተገነዘበት ጨርቅ ተምሳሌት ነው፡፡
.አንድም ጌታ ሲወለድ የተጠቀለለበት ጨርቅ ተምሳሌት ነው፡፡
#የከበሮ_ማንገቻ ጌታ አይሁድ ሲጎትቱት የነበረው ገመድ ምሳሌ ነው፡፡
.አንድም -ጌታ 6666 ጊዜ የተገረፈበት ጅራፍ ምሳሌ ነው፡፡
#ከበሮ ውስጡ ባዶ መሆኑ- የጌታችን መቃብር ምሳሌ ነው፡፡
.ከበሮ አንደኛው ገጹ ሰፊ መሆኑ - ጌታ መለኮቱ ሰፊ መሁኑ የሚያሳይ ነው፡፤
.ጌታ ሁሉን ማድረግ የሚችል አባት መሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡
.ዓለምን ሁሉ በእጁ የያዘ ፈጣሪ መሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡
#ከበሮ ሁለተኛ ገጹ ጠባብ መሆኑ - አለምን የፈጠረ ጌታ ለኛ ሲል ወደዚህ አለም በዝያች
ትንሽ የበጎች በረት ተወስኖ መወለዱ የሚያስታውስ ነው፡፡
#በከበሮ ውስጥ 7፣5፤3 ጠጠሮች ይቀመጣሉ
.7 መሆኑ- ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን
.5 መሆኑ- የአምስቱ ቅንዋተ መስቀል
.3 መሆኑ- የስላሴ ሰወስትነት
የሚገልጽ ምሳሌ ነው፡፡
#ከበሮ_ሲመታ -አይሁድ ጌታ የመቱት ያገላቱት የገረፉት ያቆሰሉት መሆኑ የሚያሳይ ምሳሌ አለው፡፡
#ከበሮ ስንመታ እነዛ ተምሳሌትዎችን በማስታወስ በማስበ ነው መምታት ያለብን፡፤ ጌታ መድኃኒዓለም በትንሳኤ ብርሃኑ በእልልታ ደስ ብሎን እንድናመሰግንበትም አድርጎናል፡፡
#ከበሮ ስናያት ምንም ላትመስለን ይሆናል ነገር ግን እንደተመልከትነው ቡዙ ተምሳሌት ያላት የቤተክርስትያናችን ክብረ ንዋያተ ቅዱሳን የመዝሙር መሳርያዎች አንዱ ነው፡፡
#ስለ_ከበሮ በመጽሃፍ ቅዱስ የተወሰነውን እንመልከት
.መዝ- 80(81)፡2- "ዝማሬን አንሱ ከበሮውን
ስጡ፡፡"
.ዳን - 3፡10 - እዮ -21፡12 - "ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ በእምብልታም
ድምጽ ደስ ይላቸዋል፡፡"
.መዝ -150፡4 - "እግዚአብሔር በከበሮ
አመስግኑ"
ከበሮ ሲመታ ቀጥ ተብሎ አይመታም፤ መዘምራን ግራና ቀኝ እያሸበሸቡ ይመታሉ ይህም ጌታ
ከሐና ቀያፋ ፤ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ ያደረገውን እንግልት ያስታውሰናል።
.ከበሮ መጀመሪያ በርጋታ ይመታና በፍጥነት ይዘዋወራል ይህም ጌታችንን አይሁድ እንደያዙት
መጀመሪያ በቀስታ እየዘበቱ
ይመቱት ነበር፤ በኋላ ግን ጲላጦስ ተመራምሮ ነፃ ሳያወጣው የሰንበት ቀንም ሳይገባብን ኑ
እንደብድበው የማለታቸው ምሳሌ ነው።
.በማሕሌት ላይ ከበሮው መሬት ላይ ተቀምጦ ሲመታ ጌታችን መሬት ላይ ወድቆ
መንገላታቱን እናስባለን።
#የከበሮ 2 ክፍሎች፦
ከበሮ ስታስቀምጡ ሁልጊዜ ሰፊው አፍ ወደ ላይ መሆን አለበት፤ ትንሹን ክፍል ወደ ላይ
ካስቀመጥን ግን ስህተት ነው።
ሰፊው የከበሮ ክፍል የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ይህም የጌታችንን የባህርይ አምላክነትና ምሉዕ
በኹለሄ መሆኑን ለሥልጣኑ ወሰን
ድንበር እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው።
ጠባቡ የከበሮ ክፍል ደግሞ የትስብእት ምሳሌ ነው፤
ይህም ጌታችን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ሥጋን ተዋህዶ መገለጡንና የዮሐንስ
ወንጌልን ያስታውሰናል፦ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ
ቃልም እግዚአብሔር ነበረ … ቃልም ሥጋ ሆነ” [ዮሐ.1-14]
#ከበሮ የሚለብሰው ልብስ አይሁድ ጌታን ያለበሱት የቀይ ከለሜዳ ምሳሌ ነው።
.በከበሮው ላይ የተጠላለፈው ጠፈር በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው።
.የከበሮው ማንገቻ አይሁድ ጌታን የጎተቱበት ገመድ ምሳሌ ነው።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለችና!!
2. ጽናጽል፡- ጸነጸለ - መታ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሸኩራ ቃጭል እንደማለት ነው፡፡ ከነሐስ፣ ከብርና ከሌሎችም ማዕድን ሊሰራ ይችላል፡፡ ጽናጽል ያማረ ድምጽ ያለው ሆኖ መልክና ልዩ ጌጥ ያለው ሲሆን በጥንት ዘመን ግብጻውያን እግዚአብሔርን ያመሰግኑበት ነበር፡፡
(መዝ150፡5) አሠራሩ ላዩ ቀስተ ደመና ይመስላል፡፡
ከታች መጨበጫው አንድ ሆኖ
የላም ምስል የነበረበት ነው፤ ዕብራውያንም ይገለገሉበት ነበር፡፡
ምሳሌነቱም፦ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጽናጽል ላይ ቀስተ ደመና መምሰሉ ‹‹እሰይም ቀስትየ በውስተ ደመና››ብሎ በተናገረው መሠረት ነው፡፡(ዘፍ 9፡12) ይህም እግዚአብሔር ለኖኅ የገባለት ቃል ኪዳን ምሳሌ ነው፡፡
አራቱ ዘንጎች በአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ቅጠሎቹ የፍጥረታት ምሳሌ ይኸውም ከአራቱ ባሕርያት የተፈጠሩትን ፍጥረታት ‹‹ሰውንም አላጠፋም ብሎ ቃል ኪዳን እንደገባ ለማሰብ›› መሰላሉ
ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ድንጋይ ተንተርሶ ያየውን መሰላል ምሳሌ ነው፡፡
(ዘፍ 28፡ 11-13)
ሁለቱ ቀጫጭን ዘንጎቹ (ጋድሞች) የመወጣጫው ምሳሌዎች ናቸው፤ ቅጠሎቹ የመላእክት ምሳሌዎች ናቸው፤ በግራና በቀኝ የቆሙት ዓምዶች የብሉይና የሐዲስ ምሳሌዎች ናቸው ፤ሁለቱ ጋድሞች የፍቅረ ቢጽና የፍቅረ እግዚአብሔር ምሳሌዎች ናቸው፡፡
3 የይሁዳን መልዕክት የፃፈው የአስቆሮቱ ይሁዳ ሳይሆን የጌታ ዘመድ የሆነው ይሁዳ ነው የበለጠ ለመረዳት የማቴዎስ ወንጌል 13÷55 ያንቡ ።
ከበሮ ፨ Kebero
English en